Wednesday, November 13, 2013

ኢትዮጵያዊነት በዐረብ ሀገራት በዓይነ ቁራኛ የሚታየው ለምንድነው?




በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚወች የተለያዩ ዓለማት ሰወች በኢትዮጵያዊነት ላይ ዘምተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሁለት ዜግነት (ኤርትራና ኢትዮጵያ) በሚል እንዲታወቅ ተግተው ከሰሩት ሐገራት መካከል በቀዳሚነት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት የዐረብ ሀገራት ናቸው፡፡ የምዕራቡ ዓለም በደም የመነገድና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ተዳክማ ስሟ ኮስሶ ለመመልከት የሚፈልጉ የጥፋት ክንዳቸውን በራሳችን ሀገር ውስጥ ኢትዮጵያዊ ተብለው ባደጉ ባንዳዎች አማካኝነት በሀገራችን በመዘርጋት ሀገራችንን ሲያሸብሩ፣ ሲከፋፍሉ፣ ሲመዘብሩ የኖሩት ምዕራባውያንና የዓረብ ሀገራት ናቸው፡፡ አሜሪካ፣እንግሊዝ፣ኢጣሊ፣ግብፅ፣ የመን፣ ሱዳን፣ ሊቢያና ሌሎቹም፡፡
የዓረቡ ዓለማት ከ60 በመቶ በላይ ክርስቲያን ሕዝብ ያለባት ሀገር በዓረብ ሀገራት መካከል መገኘት አይፈልጉም፡፡ አንድ ጊዜ በንግድ፣ ሌላ ጊዜ ደገሞ በውስጥ ለውስጥ ሽኩቻን በማነሳሳት የዐረብ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን አስረዝመው ከሺህ ሁለት መቶ ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ሲይቆረቁዟት ኖረዋል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በአስራ ሁለት ክፍል በተፃፉት የዚህ መጦመሪያ መድረክ ፅሑፎች ልትመለከቱ ትችላላችሁ፡፡ 





“እባብ ቢለሰልስ የማይናደፍ ይመስላል” ይባላል፡፡ ምንም አንድ የዐረብ ሐገር መንግስት ምንም ለኢትዮጵያ መልካም መስሎ ቢታይም ያው እባብነቱን አይለቅም፡፡ ጊዜና ቦታ ከተመቻቸለት መናደፉና መርዙን መትፋቱ አይቀርም፡፡ እንዲያውም ከአንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ ከዶ/ር አበበ ከበደ ከፃፈው አባባል እንደዋሰው ቢፈቅድልኝ፡- ዐረብ ሲተርት “እባብና ሐበሻ መንገድ ላይ ብታገኝ መጀመሪያ ሐበሻውን  ገድለህ ከዚያ እባቡን ግደል” ይላል፡፡ እኔ ሐበሻ ዐረብን በምንም ታሪክ አጋጣሚ በሀገራዊ ጉዳይ የሚያጭ፣ ኢትዮጵያም ከዐረብ ሐገራት የትኛውንም ወርራ ወይም ጦረነት ከፍታ ብሔራዊ ጥቅሙን ያሳጣችው አንድም ሀገር የለም፤ ዐረቦች ለሐበሻ እንዲህ ያለ ጥላቻ ያበቀሉት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ክርስትያን በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ጥላቻቸው ከሺህ ዘመናት በላይ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ስለመጣ ሐበሻን (ሙስሊምም ይሁን ክርስቲያን) ሁሉንም በአንድነት በጭፍን አጥብቀው ይጠላሉ፡፡


በዚህ ሁኔታ እየጠሉን ሀገራቸው ድረስ ሄድንላቸው!! አሁን ስቃይ ላይ ያሉትን ሰዎቻችንን የሸጧቸው ደላሎች ናቸው፡፡ ለዚህ ችግር መከሰት አብዛኛውን ችግር ሀላፊነቱን መውሰድ ያለብን እኛው ነን፡፡ ነገር ግን የሳውዲ መንግስት ምንም ተጠያቂነት የለበትም ማለት አይደለም፡፡ የዜግነት ክብራችንን እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነን ካላስከበርነው ማን ያከብረዋል? ስለዚህ የሳውዲ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታገስ መንግስት በዲፕሎማሲም ሆነ ባለው አማራጭ ሁሉ እርምጃ መውሰድ ግድ ይለዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ የሳውዲ ዜጎችንና ሁሉንም ሀብታቸውን በጊዜያዊነትም ቢሆን በቁጥጥር ስር ቢያውል ጫናውን የሳውዲ መንግስት ሊረዳው ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መንግስት በአስቸኳይ እነዚህን ዜጎች ማስመለሱን አጠናክሮ ቢቀጥልና በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ያለበለዚያ እንግልቱና ስቃዩ ይጨምር እንደሆን እንጅ ከዐረብ መንግስት ርህራሄ መጠበቅ ከኩርንችት መልካም የወይን ፍሬ ለማግኘት ተስፋ እንደማደረግ ያለ ይሆናል፡፡
ለመጪው ጊዜ ግን ወደ ዐረብ ሀገራት መንግስት ለዜጎቹ የሚሰጥ መተማመኛ እስካላገኘ ድረስ ምንም ዓይነት የሰወች ዝውውር ዝግ እንደሆነ ቢቆይ መልካም ነው፡፡ ማንኛችንም ብንሆን በአካባቢያችን ያሉትን ሰወች ወደ ዐረብ ሐገራት ለመሄድ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ማስተማር ማግባባትና እዚሁ ሀገራቸው ላይ ሰርተው እንዲለወጡ አማራጮችን ማሳየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ገጠር አካባቢ የመገናኛ ብዙኀን በሌለባቸው ቦታዎች ሰዎች ይህንን ዘግናኝ ሁኔታ መኖሩን ከቶ ላያውቁ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በያለንበት ሁሉ ማንኛውንም ሰው በዚህ ጉዳይ ማስተማርና ማሳመን የውዴታ ግዴታችን መሆን ይገባዋል፡፡ ሰው ሳውዲና ሌሎች ዐረብ ሀገራት ልዩነት ያለ እንዳይመስላቸው፤ “እባብ ቢለሰልስ የማይናደፍ ይመስላል” ነውና ዱባይም ይሁን ባህሬን ወይም ሌላ ቦታ ዐረብ ያው ዐረብ ነው፤ ከተመቸው ይናደፋል፡፡

Tuesday, November 12, 2013

መንግስት ጅል ሊሆን ይችላል፤ ሕዝብ ግን ከቶ ጅል ሊሆን አይችልም፡፡

ጅል መንግስት የጅል ህዝብ ው ጤት ነው ብሎ መፃፍ እጅግ የሚዘገንን ስድብ ነው፡፡ መንግስት ጅል ሊሆን ይችላል፤ ሕዝብ ግን ከቶ ጅል ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የተሳዳቢውን ጅልነት፤ እውርነት፤ ባዶነት ያሳያል፡፡ አንድ ሰው ጅል ሊሆን ይችላል፡፡ ሕዝብ ግን ከቶ ጅል አይሆንም፡፡
አንድ እጅግ ብዙ ከብቶች የነበሩት ባለፀጋ ነበር፡፡ ከብቶቹ በሙሉ እየታወኩ ሁሌ ይጨነቅ ነበር፡፡ ከዚያም የሚያደርገው የሚሰራው መፍትሔ ቢያጣ በአካባቢው ወደ ነበር አንድ ጠቢብ ሰው ጋ ሄዶ፤ ከብቶቼ ሌሊቱን ሙሉ ሲታወኩ ያድራሉ፤ ችግሩን ለይቼ ማዎቅ ተሳነኝ፤ ምን ባደርግ ይሻለኛል ብሎ ጠየቀው፡፡ ጠቢቡም በመጀመሪያ ከብቶቹን ለሁለት ከፍለህ በሁለት ጋጣ ለየብቻ አሳድራቸው፤ በአንደኛው ጋጣ ያሉት ከብቶች በሰላም ሲያድሩ ሁለተኛው ጋጣ ውስጥ ያሉት ግን ሲታወኩ ያደራሉ፡፡ አሁንም የታወኩትን ለሁለት ክፈላቸው፤ ከነዚህ አንዱ ክፍል በሰላም ማደር ሲችል ሌሎቹ ግን አሁንም መታዎካቸው ይቀጥላል፡፡ በሰላም ያደሩትን ቀደም ብሎ በሰላም ካደሩት መደቦች ጋር እየቀላቀልክ ባንድ ጋጣ አሳድራቸው፤ የሚታዎኩትን ግን አሁንም ለሁለት እየከፈልክ በሰላም የሚያድሩትን ከሰላማዊ ክፍሎች ጋር እየቀላቀልክ ጥቂት ታዋኪ ከብቶች እስኪቀሩ ድረስ ይህንን ተግባሪህን ቀጥል፡፡
መጨረሻ ላይ እነዚህን ጥቂት ከብቶች የሚያውካቸው አንድ ወይም ሁለት ከብት ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ስለዚህ ይህንን ከብት ወይ ለቅርጫ ተሸጠዋለህ፤ ወይም አርደህ ትበላዋለህ ብሎ መከረው፡፡ እንደተመከረውም አደረገ፤ በጥባጩም አንድ ከብት ብቻ ሆኖ አገኘው፡፡
ይህ የሚያሳየው ጥቂት ሰዎች በሚፈጥሩት የብላጣብልጥነት ሥራ ሀገር ልትጎዳ ትችላለች፡፡ የሕዝብ መሪም ጅል ሊሆን ይችላል፡፡ የሀገር ምንነት የማይገባው፣ ሆዱና ክብሩ ብቻ አምላኩ የሆነለት፤ የሕዝብ ስቃይና ሰቆቃ የደነደነ ልቡን ዘልቆ የማይገባ፣ ድህነት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ፤ በቤተ መንግስት ወይም ከቤተ መንግስት የሚተካከል ግቢ ውስጥ እየኖረ ከእርሱ የሚበዛ ሀብት ያላቸውን ሰዎች አይቶ እኔ እኮ ደሃ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሳይሰራ የሚበልጠው ሰው እንዲኖር እንዲፈጠርም የማይፈልግ፤ ሥልጣኑ ዘላለማዊ ለማድረግ እንደ ሄሮድስ አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ህፃናት የሚያስፈጅ (የንፁሃን ደም መፍሰስ፣ መንገላታት የማይ
ደው)፤ እንዲህ ያለ መሪ፣ እንዲህ ያለ መንግስት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ከቶ ግን ይህ የጅል ሕዝብ ውጤት አይደለም፡፡ አትሳቱ! ሕዝብ ቢታገስ ጅል አይባልም፡፡
ጅል ችግርን ሸሽቶ በስደት ጫካ ውስጥ ተደብቆ የሚያላግጥ ነው፤ ጅል አምጦ የወለደውን ሕዝብ መለሶ የሚናከስ፣ የሚሳደብ፣ የሚያሽሟጥጥ ነው፤ ጅል ችግርን በጣቶቹ እንኳን ሊነካው የማይፈልግ፤ ነገር ግን ሌሎቹ ተጋፍጠው ችግርን ከመንገዱ እንዲጠርጉለት በዚያም እርሱና ቢጤወቹ ሰላማዊ ጉዞ ያለ መሰናክል እንዲጓዙ ፈንጅ አምካኞችን ከፊቱ እንዲሔዱለት በርቀት ሆኖ የሚያግባባ፣ የሚያሽቃብጥ ነው፡፡
ሕዝብ ግን ችግርን እየተጋፈጠ፤ እየታገሰ፤ እያለዘበ፣ እያዋዛ፤ እያለሰለሰ ፈንቅሎ ይጥለዋል እንጅ ትቶት አይሸሽም፡፡ ሌላ ሦስተኛ ወገን ችግርን ከትክሻዬ ያነሳልኛል ብሎ አይጠብቅም፡፡