Wednesday, November 13, 2013

ኢትዮጵያዊነት በዐረብ ሀገራት በዓይነ ቁራኛ የሚታየው ለምንድነው?




በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚወች የተለያዩ ዓለማት ሰወች በኢትዮጵያዊነት ላይ ዘምተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሁለት ዜግነት (ኤርትራና ኢትዮጵያ) በሚል እንዲታወቅ ተግተው ከሰሩት ሐገራት መካከል በቀዳሚነት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት የዐረብ ሀገራት ናቸው፡፡ የምዕራቡ ዓለም በደም የመነገድና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ተዳክማ ስሟ ኮስሶ ለመመልከት የሚፈልጉ የጥፋት ክንዳቸውን በራሳችን ሀገር ውስጥ ኢትዮጵያዊ ተብለው ባደጉ ባንዳዎች አማካኝነት በሀገራችን በመዘርጋት ሀገራችንን ሲያሸብሩ፣ ሲከፋፍሉ፣ ሲመዘብሩ የኖሩት ምዕራባውያንና የዓረብ ሀገራት ናቸው፡፡ አሜሪካ፣እንግሊዝ፣ኢጣሊ፣ግብፅ፣ የመን፣ ሱዳን፣ ሊቢያና ሌሎቹም፡፡
የዓረቡ ዓለማት ከ60 በመቶ በላይ ክርስቲያን ሕዝብ ያለባት ሀገር በዓረብ ሀገራት መካከል መገኘት አይፈልጉም፡፡ አንድ ጊዜ በንግድ፣ ሌላ ጊዜ ደገሞ በውስጥ ለውስጥ ሽኩቻን በማነሳሳት የዐረብ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን አስረዝመው ከሺህ ሁለት መቶ ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ሲይቆረቁዟት ኖረዋል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በአስራ ሁለት ክፍል በተፃፉት የዚህ መጦመሪያ መድረክ ፅሑፎች ልትመለከቱ ትችላላችሁ፡፡ 





“እባብ ቢለሰልስ የማይናደፍ ይመስላል” ይባላል፡፡ ምንም አንድ የዐረብ ሐገር መንግስት ምንም ለኢትዮጵያ መልካም መስሎ ቢታይም ያው እባብነቱን አይለቅም፡፡ ጊዜና ቦታ ከተመቻቸለት መናደፉና መርዙን መትፋቱ አይቀርም፡፡ እንዲያውም ከአንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ ከዶ/ር አበበ ከበደ ከፃፈው አባባል እንደዋሰው ቢፈቅድልኝ፡- ዐረብ ሲተርት “እባብና ሐበሻ መንገድ ላይ ብታገኝ መጀመሪያ ሐበሻውን  ገድለህ ከዚያ እባቡን ግደል” ይላል፡፡ እኔ ሐበሻ ዐረብን በምንም ታሪክ አጋጣሚ በሀገራዊ ጉዳይ የሚያጭ፣ ኢትዮጵያም ከዐረብ ሐገራት የትኛውንም ወርራ ወይም ጦረነት ከፍታ ብሔራዊ ጥቅሙን ያሳጣችው አንድም ሀገር የለም፤ ዐረቦች ለሐበሻ እንዲህ ያለ ጥላቻ ያበቀሉት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ክርስትያን በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ጥላቻቸው ከሺህ ዘመናት በላይ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ስለመጣ ሐበሻን (ሙስሊምም ይሁን ክርስቲያን) ሁሉንም በአንድነት በጭፍን አጥብቀው ይጠላሉ፡፡


በዚህ ሁኔታ እየጠሉን ሀገራቸው ድረስ ሄድንላቸው!! አሁን ስቃይ ላይ ያሉትን ሰዎቻችንን የሸጧቸው ደላሎች ናቸው፡፡ ለዚህ ችግር መከሰት አብዛኛውን ችግር ሀላፊነቱን መውሰድ ያለብን እኛው ነን፡፡ ነገር ግን የሳውዲ መንግስት ምንም ተጠያቂነት የለበትም ማለት አይደለም፡፡ የዜግነት ክብራችንን እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነን ካላስከበርነው ማን ያከብረዋል? ስለዚህ የሳውዲ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታገስ መንግስት በዲፕሎማሲም ሆነ ባለው አማራጭ ሁሉ እርምጃ መውሰድ ግድ ይለዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ የሳውዲ ዜጎችንና ሁሉንም ሀብታቸውን በጊዜያዊነትም ቢሆን በቁጥጥር ስር ቢያውል ጫናውን የሳውዲ መንግስት ሊረዳው ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መንግስት በአስቸኳይ እነዚህን ዜጎች ማስመለሱን አጠናክሮ ቢቀጥልና በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁሉንም ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ያለበለዚያ እንግልቱና ስቃዩ ይጨምር እንደሆን እንጅ ከዐረብ መንግስት ርህራሄ መጠበቅ ከኩርንችት መልካም የወይን ፍሬ ለማግኘት ተስፋ እንደማደረግ ያለ ይሆናል፡፡
ለመጪው ጊዜ ግን ወደ ዐረብ ሀገራት መንግስት ለዜጎቹ የሚሰጥ መተማመኛ እስካላገኘ ድረስ ምንም ዓይነት የሰወች ዝውውር ዝግ እንደሆነ ቢቆይ መልካም ነው፡፡ ማንኛችንም ብንሆን በአካባቢያችን ያሉትን ሰወች ወደ ዐረብ ሐገራት ለመሄድ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ማስተማር ማግባባትና እዚሁ ሀገራቸው ላይ ሰርተው እንዲለወጡ አማራጮችን ማሳየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ገጠር አካባቢ የመገናኛ ብዙኀን በሌለባቸው ቦታዎች ሰዎች ይህንን ዘግናኝ ሁኔታ መኖሩን ከቶ ላያውቁ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በያለንበት ሁሉ ማንኛውንም ሰው በዚህ ጉዳይ ማስተማርና ማሳመን የውዴታ ግዴታችን መሆን ይገባዋል፡፡ ሰው ሳውዲና ሌሎች ዐረብ ሀገራት ልዩነት ያለ እንዳይመስላቸው፤ “እባብ ቢለሰልስ የማይናደፍ ይመስላል” ነውና ዱባይም ይሁን ባህሬን ወይም ሌላ ቦታ ዐረብ ያው ዐረብ ነው፤ ከተመቸው ይናደፋል፡፡

No comments:

Post a Comment